ጥር 6/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ አንድ ቢሊዮን ሊትር የማጣራት አቅም ያላቸው ስምንት የነዳጅ ማጣሪያ ታንከሮችን በሀገሪቱ እየገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡
"ከውጭ ሀገር የነዳጅ ድፍድፍ ማስገባት ከሀገር ውስጥ ከመግዛት የተሻለ ሲሆን፤ የሀገር ውስጥ ክምችትን ለመጨመር ያስችላል" ነው የተባለው፡፡
በዚህ ረገድ በናይጄሪያው ዳንጎቴ የነዳጅ ማጣሪያ አንድ ቢሊዮን ሊትር የማጣራት አቅም ያላቸው 8 ታንከሮችን እየገነባሁ ነው ሲል አስታውቋል፡፡
የዳንጎቴ ኢንዱስትሪዎች ምክትል ፕሬዝዳንት ዴቫኩማር ኤድዊን "አሁን ላይ ያሉት 20 የነዳጅ ማጣሪያዎች፤ 2 ነጥብ 4 ቢሊዩን ሊትር የማጣራት አቅም አላቸው" ብለዋል፡፡
ተጨማሪ የማጣሪያዎቹ ግንባታ ሲጠናቀቅ በጠቅላላ ወደ 3 ነጥብ 4 ቢሊዩን ሊትር ወይንም በ41 ነጥብ 67 በመቶ ከፍ እንደሚያደርገው መናገራቸውን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
"ይህ የነዳጅ የማጠራቀሚያ ለናይጄሪያ አስፈላጊ ነው" ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ከስምንቱ ታንኮች ውስጥ የአራቱ ግንባታ መጠናቀቁን አስረድተዋል።