ጥር 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ)በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ በነዳጅ ጫኝ ታንከር ላይ በደረሰ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 98 መድረሱን የሀገሪቱ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ፍንዳታው የተከሰተው ቅዳሜ ረፋድ ላይ በኒጀር ግዛት ሱሌጃ አካባቢ ሲሆን፤ የነዳጅ ጫኝ ታንከር ውስጥ ግለሰቦች በጄነሬተር ተጠቅመው ቤንዚን ወደ ሌላ መኪና ለማዛወር ሙከራ በማድረጋቸው መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በዚህም ነዳጁን ሲያስተላልፉ የነበሩ እና በአካባቢው የነበሩ ሌሎች በርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የብሔራዊ ድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ኤጀንሲ የኒጀር ግዛት የሥራ ኃላፊ ሁሴኒ ኢሳህ የሟቾች ቁጥር ከዚም ሊጨምር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል።

ኃላፊው አክለውም በአደጋው ወቅት በቦታው ተገኝተው ፎቶግራፎችን ሲያነሱ የነበሩ እና ሌሎች ቤንዚን ለመውሰድ ሲሞክሩ የነበሩ ግለሰቦች በፍንዳታው ተጎጂ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ