የካቲት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ጣይቱ ክፍለ ከተማ በአንድ ጋራዥ ላይ ሌሊት 10፡30 በደረሰ የእሳት አደጋ 13 ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።
የክፍለ ከተማው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መርማሪ ዋና ሳጅን ፋኖስ አንዳርጌ ለኤፍ ኤም ሲ እንደገለጹት፤ ይማም በተባለ ጋራዥ ላይ ባጋጠመ የእሳት አደጋ ምክንያት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል።

ማህበረሰቡና በከተማዋ የሚገኙ የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች ባደረጉት ርብርብ አሁን ላይ እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል ብለዋል።
የእሳት አደጋው ሁለት ጋራዦች ላይ የተነሳ ሲሆን፤ በጋራዦቹ ውስጥ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች ውድመት እንደደረሰባቸው ነው የተገለጸው።

የአደጋውን መንስኤ እና በአደጋው የደረሰውን ውድመት መጠን ለማጣራት የምርመራ ሥራ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ