የካቲት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ በተጀመረው 46ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛ የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በተካሄደው ምርጫ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመርጣለች።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም እድገት ዙሪያ እያበረከተችው ላለው አስተዋጽኦ እውቅና የሚሰጥ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባል ሆና ተመረጠች
