የካቲት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በቅርቡ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የፕሮቶኮል ተጠባባቂ ሹም አቢ ጆንስ አቅርበዋል።
አምባሳደሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ውይይት፤ የኢትዮጵያን እና የአሜሪካን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
አቢ ጆንስ በበኩላቸው፤ አምባሳደሩ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በሚያከናውኑት ተግባራት አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንደሚያደርጉ መግለጻቸውን በዋሺንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ቅጂ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አቀረቡ
