ጥር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ ጥር 19 ቀን 2017 ንዝረቱ አዲስ አበባ እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የተሰማና ከፍተኛ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት አዋሽ አካባቢ ተከስቷል፡፡
ዛሬ 4:40 ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.9 ሆኖ ተመዝግቧል።
የመሬት መንቀጥቀጡ ንዝረት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እንዲሁም በክልል ከተሞች ላይ የተሰማ ሲሆን፤ ንዝረቱ ከበድ እና ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ እንደነበር በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ የአሐዱ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ከደቂቃዎች በፊት ተከሰተ
