ጥር 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዛሬው ዕለት 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላን መረከቡን አስታውቋል፡፡

አውሮፕላኑ የካርጎ ጭነት አገልግሎት አድማስን ለማሳደግ የራሱ አስተዋፅዖ ከማበርከቱ በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ የራሱ አስተዋፅዖ እንደሚኖረውም አስታውቋል።

Post image

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን የላቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

አዲሱ የካርጎ አውሮፕላንም አየር መንገዱ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን የሚያግዙና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ውስጥ ይዞ መምጣቱ አየር መንገዱ አስታውቋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ