ጥር 28/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ዛሬ ጥር 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:30 በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ሕንጻ ውስጥ ወደ በረራ ይዞ መግባት ከሚከለከሉ ቁሳቁሶች መካከል ከመንገደኞች የሚሰበሰብ የሲጋራ መለኮሻ (ላይተር) ጊዜያዊ የማስቀመጫ ስፍራ ውስጥ፤ ጭስ መከሰቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል፡፡

በዚህም ምክያት ለመንገደኞች ደህንነት ሲባል ሕንጻው ለጊዜው አገልግሎት ማቋረጡን ገልጿል።

"በመሆኑም በዛሬው ዕለት ወደ ሀገር ውስጥ መዳረሻዎቻችን የምትጓዙ መንገደኞቻችን በዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በኩል ወደ በረራችሁ እንድትሳፈሩ እናሳስባለን" ብሏል አየር መንገዱ ባወጣው መግለጫ፡፡

ከነገ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተለመደው የሀገር ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት መስጠት እንደሚቀጥል ያስታወቀው አየር መንገዱ፤ ለተፈጠረው መጉላላት መንገደኞቹን ይቅርታ ጠይቋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ