መጋቢት 11/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢፊደሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት የ2017 የግማሽ ዓመት አፈጻጸምን አስመልክተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ ከምክር ቤት አባላትም ጥያቄዎች ተነስቷል፡፡
"ችግሮችን በጠመንጃ ለመፍታት መሞከር ሀገሪቱን ወደ ማትወጣው ቀውስ ውስጥ ሊስገባት ይችላል" ሲሉ የተናገሩት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የምክር ቤቱ አባሉ ደ/ር ደሳለኝ ጫኔ ናቸው፡፡
"አሁን ያሉትን ችግሮች መፍታት የሚቻለው በሀሳብ ልዕልና ብቻ ነው" ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
በተለያዩ ቦታዎች ባሉት ግጭቶች ዜጎች ሕወታቸውን ማጣታቸውን እና በርካቶች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ዓመታት በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያ እንዲም ቤንሻንጉል ክልል ያሉት የጸጥታ ችገሮች ኢኮኖሚው የሚፈለገውን ያህል እንዳያድግ እንቅፋት መሆኑንም አንስተዋል፡፡
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩትም እንዲፈቱ ሲሉም የምክር ቤት አባሉ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ጠይቀዋል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
"ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር መፍታት የሚቻለው በሀሳብ ልዕልና ብቻ ነው" ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ
