ጥር 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የሚሰሩ ሕንጻዎች አካል ጉዳተኞችን ያማከሉ ባለመሆናቸው ለችግር እያጋለጡ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በየከተሞች እየተገነቡ ያሉ ሕንጻዎችን በተመለከተ አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረገ አሰራር እንዲኖር፤ ከሚመለከተዉ አካል ጋር በመሆን እየሰተራ ነው ተብሏል፡፡
ሆኖም አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያላደረገ ግንባታ ሲኖር እርምጃ የሚያስወስድ የሕግ አስራር አለመጽደቁ ክፍተት እንደፈጠረባቸው፤ በሚኒስቴሩ የማህበራዊ ተሃድሶ ከፍተኛ ባለሙያ ሆኑት አቶ ሙሐመድ ከድር ለአሐዱ ተናግረዋል።
ከሕንጻ ግንባታዎች ጋር በተያያዘ አካል ጉዳተኞች በተደጋጋሚ ቅሬታ እያነሱ መሆኑን ባለሙያው ገልጸዋል፡፡
"ችግሩን ለመፍታትም እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ ነው" ሲሉም ገልጸዋል።
አክለውም በሚገነቡ ሕንጻዎች ላይ ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥ በአካል ጉዳተኞች ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እየፈጠረ መሆኑንና በማህበረሰቡ ላይ ያለው አመለካከትም ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።