መጋቢት 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሪል እስቴት ዘርፉ ላይ በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኘው ኦቪድ ሪል እስቴት በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ያዘጋጀውን የአፍጥር ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የአፍጥር ፕሮግራሙ ሦስት አላማዎች እንዳሉት የተገለጸ ሲሆን፤ የመጀመሪያው ከሙስሊም ወንድም እህቶች ጋር ኢፍጣር ማካፈል፣ ሁለተኛው ደግሞ ኦቪድ ሪል ስቴት በኦቪድ ገላን ጉራ ከተማ ከሚገነባው መንደሮች አንዱ የሆነውን የኦቪድ ነጃሽ መንደርን መገንባት መጀመሩን ማብሰር እንዲሁም ቤቶችን ለሚገዙ ደንበኞች የሸሪዓውን ሕግ ለማስተግበር የሚያስችል ዳይሬክቶሬት መዘጋጀቱን ለመግለፅ መዘጋጀቱን የኦቪድ ሪል ስቴት ማርኬቲንግ ማናጀር ወይዘሪት መቅደስ ቀደመ ተናግረዋል።

አክለውም ኦቪድ "እስላሚክ ፋይናንሽያል ሲስተም"ን ወደ ተግባር ለማስገባት ከተለያዩ ባለሙያዎች እና የሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት ጋር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ኦቪድ ሪል ስቴት የሙስሊሙን ማህበረሰብ ማዕከል ያደረገውን መንደሩ ሲገነባ፤ በውስጡ መስጂዶች እና ሌሎችም መሰረታዊ ጉዳዮችን ለማካተት እንዳቀደም ወይዘሪት መቅደስ አስረድተዋል።

በተለይም በዚህ የረመዳን ወር የኢድ ኤክስፖ ላይ በመሳተፍ ቤት ገዝተው መቶ ከመቶ ለሚከፍሉ፤ የ5 ከመቶ እና 50 ከመቶ ለሚከፍሉት ደግሞ የ3 ከመቶ ቅናሽ ለማድረግ መታሰቡን ተናግረዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ