የካቲት 5/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ3 ሚሊየን 52 ሺሕ 904 ብር በላይ የሚገመት የዘይትና ስኳር መውረሱን የየካ ክፍለ ከተማ የሕገ-ወጥ ንግድ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ-ሃይል አስታውቋል።

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚር ከሊፋ እንደገለጹት ከፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ንግድ ተቋም በክፍለ ከተማው ሕገ-ወጥ ንግድ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ-ሃይል በተደረገ ክትትል በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው የዘይትና ስኳር ተወርሷል።

Post image

አቶ አሚር አክለውም በፍተሻው ወቅት 149 ባለ 20 ሊትር ዘይት እና 304 ኩንታል ስኳር መያዙን ተናግረዋል።

Post image

የተወረሱት ንብረቶችም በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በማከፋፈል ህብረተሰቡ እንዲጠቀምበት መደረጉን የጽ/ቤት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ