ጥር 16/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የፌደራል ፓሊስ ከ2010 ዓ.ም ከነበረው የፓሊስ ሀይል አሁን ላይ ያለው የፓሊስ ቁጥር በ100 መቶ እጥፍ መጨመሩን ገልጿል።
በዚህም ለበርካታ ዓመታት የፓሊስ ማሰልጠኛ የነበረው የፓሊስ ኮሌጅ ወደ ኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርስቲ ማደጉን ነው ያስታወቀው።
የፌደራል ፓሊስ ይህንን ያለው ባለፉት ዓምስት ዓመታት የተከናወኑ የማዕከል ማሻሻያ ሥራዎችን ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኋን ተቋማት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ባስጎበኘበት ወቅት ነው።
የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ በፓሊስ ትምህርትና ስልጠና ሀገሪቱን በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና የፓሊስ አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ተብሏል።
በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ዓለም አቀፍ የምርምር ሥራዎችን መስራት የሚያስችል የፎረንሲክ ኢንስቲትዩት ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።
ለዚህም ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት እንዲቻል በአንድ ጊዜ 10 ሺሕ ሰዎችን ለማሰልጠን የሚያስችል ዘመናዊ የፓሊስ ማሠልጠኛ ተቋም በግንባታ ላይ መሆኑ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ፓሊስ ዩኒቨርሲቲ የፓሊስ ትምህርትና ስልጠና፣ ጥናትና ምርምር፣ የማማከርና የማህበረሰብ አገልግሎት እየሰሠጠ መሆኑ ተገልጿል።
በተጨማሪም የተለያዩ የትምህርት አይነቶችን በሁለተኛ ዲግሪ ደረጃ ከሀገር ውስጥ ዜጎች ባለፈም ለአፍሪካ ሀገራትም የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ተችላል ተብሏል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ