ጥር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከነገ ጥር 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጣጫ መንገዶቹ ላልተወሰኑ ቀናት ዝግ እንደሚሆን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በአዲስ አበባ ከተማ በ2ኛው ዙር ከሚለሙት የኮሪደር መስመሮች መካከል የሲሚት- ጎሮ መንገድ አንደኛው መሆኑ አስታውሷል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የሲ ኤም ሲ- ፔፕሲ - ጎሮ - መንገድ ልዩ ቦታው ሳፋሪ መብራት አካባቢ ብሪቲሽ ትምህርት ቤት አጠገብ የመንገድ ቆረጣ እንደሚከናወን ገልጿል።
በዚህም መሰረት ከነገ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከፊጋ - ወደ ሳፋሪ እንዲሁም ከሳፋሪ -ወደ ፊጋ የሁለቱም አቅጠጫ መንገዶቹ ዝግ እንደሚሆኑ ገልጿል።
በመሆኑም አሽከርከሪዎች ይህንን አውቀው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አሳስቧል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ