ጥር 15/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።
ምክር ቤቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት መሰረት የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የእጩዎች ሲመለምል መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን፤ ለዋና ዳይሬክተርነት 60 ግለሰቦች፣ በምክትል ዋና ዳይሬክተርነት 200 እንዲሁም በዘርፍ እምባ ጠባቂ 85 ግለሰቦች በእጩነት ከቀረቡ መቅረባቸው ተመላክቷል።
በዚህም መሰረት ምክር ቤቱ ከቀረቡለት እጩዎች ውስጥ፤ ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በቀጣይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ ሹመት ሰጥቷቸዋል።
በተጨማሪም ዶ/ር የኔነህ ስመኝ የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም በምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዲመሩ እንዲሁም፤ አቶ አባይነህ ኦዳቶ የዘርፍ እምባ ጠባቂ ሆነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ