ጥር 26/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድሥት ወራት 245 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ፤ ጠቅላላ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑን ከ1 ነጥብ 4 ትሪሊዮን ብር በላይ ማድረስ መቻሉን አስታውቋል፡፡

ይህ አፈፃም ከእቅድ አንፃር 147 ነጥብ 6 በመቶ አፈፃፀም የተመዘገበበት መሆኑን ነው ባንኩ የገለጸው፡፡

Post image

ዛሬ በተጀመረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀው፤ ባንኩ በግማሽ ዓመት ያሰባሰበው የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በተመሳሳይ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተሰበሰበው ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ ብር 423 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር ውስጥ 58 ነጥብ 3 በመቶ ድርሻ እንዲኖረው ያስቻለ ነው፡፡

በተጨማሪም ባንኩ በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሰባት ወራት ከ303 ቢልዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም በባንኩ ታሪክ የተመዘገበ ትልቁ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን በመሆን ተመዝግቧል።

Post image

በባንኩ የተመዘገበው ይህ ውጤት ደንበኞች ከባንኩ ጋር ያላቸው ግንኙነት እና የባንኩ የአገልግሎት ጥራት መሻሻል ማሳያ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በዚህም ባንኩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማንቀሳቀስ የተጣለበትን ትልቅ ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚያግዘው ተጠቁሟል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ