የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት አዲስ አበባ ላይ ባሳላፍነው ሳምንት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ እየገቡ መሆኑን፤ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

Post image

ሰሞኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራር ጋር ተፈራረምኩት ያለውን የሰላም ስምምነት የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ያጣጣለው ሲሆን፤ "የክልሉ መንግሥት የሰላም ስምምነት ተፈራረምኩ ያለው ከወራት በፊት ከቡድኑ ከተባረሩ አንድ ግለሰብ ጋር ብቻ ነው ሲል" መግለጹ ይታወሳል።

ከመንግሥት ጋር የጀመረውም ሆነ ያቀደው አዲስ የሰላም ድርድር እንደሌለ የጠቀሰው ቡድኑ፤ "መንግሥት ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር እየተደራደርኩ ነው በማለት የሚናገረው "ሕዝብን ለማወናበድ" ሲል ብቻ ነው" በማለት ከሶም ነበር።

ይህንን ሥምምነት ተከትሎም በዛሬው ዕለት በምዕራብ ሸዋ ዞን ኮቢ ወረዳ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራር አባላት በሕዝብ አቀባበል እንደተደረገላቸው ተነግሯል።