ጥር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው የ4ኛ ዓመት 6ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው የሀገሪቱን ዲፕሎማሲ ታሳቢ ያደረገ የኤምባሲዎች የመሬት ጥያቄን እና የከተማዋን የኢኮኖሚ እንቅቃሴ ለሚያጎለብቱ፣ ሰፊ የሥራ እድል እየፈጠሩ ላሉ፣ የውጪ ምንዛሬ እያስገኙ ላሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረቻ ማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎችን መርምሮ ውሳኔ ማሳለፉን ከከንቲባ ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ