ጥር 19/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤውን "ከቃል እስከ ባህል" በሚል መሪ ቃል ከጥር 23 - 28 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በአድዋ ድል ሙዚየም ይካሄዳል።
በዚህም ፓርቲው በሚያካሂደው ጉባኤ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች የሚጠበቁ ውሳኔዎችን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።
የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የዋና ጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በሰጡት መግለጫ፤ በጉባኤው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የኢንስፔክሽን እና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን እንዲሁም የጉባኤ ተሳታፊዎች በአጠቃላይ 1 ሺሕ 700 የሚሆኑ ሰዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
እንዲሁም በጉባኤው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና 15 የሚሆኑ የውጭ ሀገራት እህት ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ አንስተዋል።
"ጉባኤው ፓርቲውን እና መንግስትን የሚያጠናክሩ ውሳኔዎች እና የሀገርን ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችና የውሳኔ ሀሳብ የሚቀመጡበት ነው" ብለዋል።
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ