ጥር 9/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) 7ኛ ዙር ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ ከ1 ዓመት ያላነሰ ጊዜ የቀራት ኢትዮጵያ ምርጫን የሚያሳልጥ ተቋም የሚመራበትን አዋጅ ሊያሻሽል መሆኑን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬዉ ዕለት አስታውቋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነምግባር አዋጁ ቁጥር 1162/2011 ማሻሻያ lማድረግ ማሰቡን ገልጿል።

ቦርዱ አዋጁን የሚያሻሽለዉ የአዋጁን አፈፃፀም እና አተገባበር ላይ የታዩ ክፍተቶችን እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን ከግምት በማስገባት እና በተሰጠው ኃላፊነት መሆኑን አመላክቷል።

በመሆኑም ቦርዱ ባዘጋጀዉ ረቂቅ አዋጅን በሚመለከትም ከፖለቲካ ፖርቲ አመራሮች፣ የመገናኛ ብዙኃን እና ሌሎች ባለድርሻዎች ጋር ውይይት አካሂዷል።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢሜላትወርቅ ሀይሉ በዚህ አዋጅ ሥር ሦስት ሕዝበ ውሳኔ እና አንድ ብሔራዊ ምርጫ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል።

ማሻሻያዉን በዚህ ዓመት መጀመሩን የገለጹ ሲሆን፤ 1162/2011 አዋጅን ለማሻሻል ያሉ ክፍተቶችን ላይ በርካታ ውይይት ከተካሄደበት በኃላ ክፍተቶችን ለመሙላት በማሰብ የተደረ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ቅሬታ ሲያነሱ የነበሩ ፖርቲዎችና ጉዳያቸውን ፍርድ ቤት ድረስ ያደረሱት ጋር ያለውን ክፍተት ለመመልከት የሚረዳ መሆኑንም ዋና ሰብሳቢዎ ተናግረዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ስድስት ዓመታትን የቆየውን አዋጅ ለመሻሻል ከፖርቲዎች በተጨማሪ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይ ውይይት እንደሚያደርግ ተገልጿል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ