ጥር 10/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱና አፈጉባኤው ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከጎንደር ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
![Post image](/_image?href=https%3A%2F%2Fcdn.sanity.io%2Fimages%2Fbede4k7t%2Fproduction%2Fb8b391466652dba71239f6847f3f536d58bd2a47-1080x720.jpg&w=1080&h=720&f=webp)
በተጨማሪም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የጥምቀት በዓልን ለማክበር ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ የደረሱ ሲሆን፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኜው እና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
![Post image](/_image?href=https%3A%2F%2Fcdn.sanity.io%2Fimages%2Fbede4k7t%2Fproduction%2F72fd0a6369479ccbd9949793504a5bafc201043f-1080x720.jpg&w=1080&h=720&f=webp)