የካቲት 14/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደማህበረሰቡ ለተቀላቀሉ ሦስት የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ኦነግ ሸኔ) አመራሮች ሹመት ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት፦

1. በትግል ሥማቸው (ጃል ሰኚ) በመባል የሚታወቁት አቶ ያደሳ ነጋሳ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች አማካሪ

2. አቶ ኦሮሚያ ረቡማ፦ የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ ምክትል ኃላፊ

Post image

3. አቶ ቶሌራ ረጋሳ፦ የኦሮሚያ ክልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው መሾማቸውን ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Post image

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ