ጥር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በማይጨው ለምለም ካርል ሆስፒታል ከአንዲት እናት 20 ነጥብ 6 ኪሎ ግራም የሚመዝን አላስፈላጊ ዕጢ መወገዱን ሆስፒታሉ ገለፀ።
ታካሚዋ የቦራ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት የ63 ዓመት የዕድሜ ባለ ፀጋዋ ወይዘሮ ካሱ ረዳኢ ናቸው።

በማህጸናቸው የእንቁላል ማምረቻ አካል ውስጥ በተፈጠረ አላስፈላጊ ዕጢ ምክንያት ወደ ሆስፒታሉ ያመሩ ሲሆን፤ አንድ ሰዓት ተኩል በወሰደ የተሳካ ከባድ ቀዶ ጥገና ላለፉት 5 ዓመታት አብሯቸው የቆየው ዕጢ እንደተወገደላቸው ኢብኮ ዘግቧል።
የቀዶ ጥገና ቡድኑ በማህፀንና የወሊድ ስፔሻሊስት ዶ/ር አክሊል አለማየሁ መመራቱ ተገልጿል፡፡
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ