ጥር 25/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የገዢው ብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐብይ አሕመድን (ዶ/ር) የፓርቲው ፕሬዝዳንት አድርጎ በከፍተኛ ድምጽ መርጧቸዋል።

ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

Post image

በተያያዘ ዜና ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መምረጡ ተገልጿል።

ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ