ጥር 13/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኘው ደም ባንክ ከለጋሾች በሚሰበሰብ ደም ከሀገር አቀፍ ደረጃ ከቀዳሚዎቹ ተርታ ይሰለፍ የነበረ ቢሆንም፤ በአሁን ሰዓት ከፍተኛ የደም እጥረት እንደገጠመው አስታውቋል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶች፣ ሕጻናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልሰው ጫንያለው ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ የደም ባንኩ በክልሉ ባለው የጸጥታ እና የእንቅስቃሴ ችግር ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ዩኒት ደም መሰብሰብ እየቻለ አይደለም፡፡

አሐዱም የክልሉን መረጃ መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያ ደም ባንክን የጠየቀ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሀብታሙ ታየ በሰጡት ምላሽ፤ "የባህር ዳር ደም ባንክ በ6 ወር አፈፃፀም ለመሰብሰብ ካቀደው ማሳካት የቻለው 87 በመቶ የሚሆነውን ነው" ብለዋል፡፡

አክለውም የከተማው ደም ባንክ በተለይ በዚህ ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ከማኅበረሰቡ በቂ ደም እንዳይሰበሰብ በክልሉ ያለው የፀጥታ ችግር ትልቅ ተግዳሮች መሆኑንም አንስተዋል፡፡

#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ